ኤፍ ኢ ኢም የግዥና አቅርቦት አገልግሎት ኃ.የተ.ግ.ማህበር በተሰማራበት ዘርፉ የረጅም ግዜ ልምድ እና ከፍተኛ ዕውቀት ባላቸው ባለሞያዎች የተመሰረተ እና በተለይ ጨረታ ላይ ልዩ ትኩረት ያደረጉ ለተጠቃሚዎች የላቀ ጠቀሜታ ያላቸው አዳዲስ አገልግሎቶችን ጭምር በማስተዋወቅ እና በመስጠት በሀገራችን ፈር-ቀዳጅ ኩባንያ ነው፡፡ ጨረታ ከፍተኛ ግብይት የሚፈጸምበት ዋነኛ ዘዴ እንደ መሆኑ መጠን፤ አቅራቢ ድርጅቶች የጨረታ ማስታወቂያዎችን በአሉበት-ቦታ ሆነው በዚህ አዲስ-ጨረታ በተሰኘ ድረ-ገጹ ከአንድ ቋት በየዕለቱ እንዲያገኙ ከማስቻል ጎን-ለጎን በቀላሉ ከዛው ላይ ትዕዛዝ በማስተላለፍ የሚፈልጉት የጨረታ-ሠነድን ማስገዛት የሚያስችላቸው አሰራር አብሮ ዘርግቷል፡፡ በዚሁ መሰረት በርካታ አቅራቢ ከሃገራችን የተለያዩ አካባቢዎች የጨረታ ሠነድ ለማኘትም ሆነ ሔዶ ለመጫረት የነበረባቸው ውጣ ውረድ በመረዳት፤ ከ420 በላይ ከተሞችን ተደራሽ ያደረገ አስተማማኝ የሎጂስቲክስ ኔት ወርክን በመፍጠር፤ የጨረታ ሠነድ ገዝቶ ከማቅረብ እና መወዳደሪያ ኤንቬሎፕ ተረክቦ ከማድረስ በተጨማሪ፤ በጨረታ ያሸነፉትን ዕቃ ጭምር አጓጉዞ የማስረከብ አገልግሎት አጣምሮ የሚሰጥ የመጀመሪያው ድርጅት ነው፡፡

ለደንበኞቹ የላቀ ስኬት የሚተጋው ድርጅታችን፤ በጨረታ ውድድር የተሻለ ውጤታማ ለመሆን የሚጠቅሙ ስልጠናዎችን አዘጋጅቶ የሚሰጥ ከመሆኑ በተጨማሪ፤ የጨረታ ቴክኒክ መወዳደሪያ ሠነድ ዝግጅትን ጨምሮ ተያያዥ የሆኑ የምክር እና ሙያዊ አገልግሎቶች በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡ ዕውቀትን ከቴክኖሎጂ ጋር አጣምረን የምንሰጠው አገልግሎት ተጠቃሚዎች ወጪያቸውን ቀንሰው፤ ግዜያቸውን ቆጥበው፤ የገበያ አድማሳቸውን ይበልጥ በማስፋት በተለያዩ አካባቢዎች በቀላሉ ተደራሽ እንዲ ሆኑ የላቀ አስተዋፀዎ በማድረግ ላይ እንገኛለን፡፡  

 

ተልዕኳችን፡-   

በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዙ ፈጣን እና ቀልጣፋ አገልግሎቶችን በመስጠት፤ ደንበኞቻችን በአሉበት ቦታ ሆነዉ ምርትና አገልግሎታችዉን በመላዉ ሀገራችን እንዲያቀርቡ ማገዝ ነዉ፡፡

ራዕያችን፡-

በአቅራቢዎችና ግዥ-ፈጻሚ አካላት መካከል ያለዉ የንግድ ልዉዉጥ በቦታና የግዜ ውሱንነት እንዳ ይገደብ ማስቻል ነው፡፡